About

 
 

የማየውን ታያለህን?

ብዙውን ጊዜ ዓይናችን ሥር ያለውን ነገር ማየት ይሳነናል፡፡ እውን የሆኑ የዕለት ተዕለት የኑሮ ክስተቶችን ወይም የሕይወት እንቅስቃሴዎችን ሳናስተውል የምንቀርባቸው በርካታ ምክንያቶች አሉ። ምናልባት በኑሮ ሩጫ ስለምንያዝ፤ አሊያም ደግሞ በየጊዜው ልናስተውለው ከምንችለው በላይ የእይታ መረጃ ስለሚገጥመን ሊሆን ይችላል። ምናልባትም ከባለፈው የሕይወት ተሞክሮአችን በመነሳት በመንገዳችን ላይ ሁሉ የሚገኙ ክስተቶችን እና እውነቶችን እናውቃቸዋለን ብለን ስለምናስብም ይሆናል። ምክንያታችን ምንም ይሁን ምን ዕለት ከዕለት በሚገጥሙን እይታዎች ላይ ያለን ቸልተኝነት በፍጹም የማይካድ ሐቅ ነው። በመሆኑም ዘመናዊው የፎቶግራፍ ሙያ በውጤቶቹ አካባቢያችንን በሚገባ የምንመለከትበት እና የምንረዳበት ሁነኛ መሣሪያ ሆኖ እናገኘዋለን።

ፎቶግራፍ አዳኙ ካሜራ ሁነኛ ነው ብሎ ያሰበውን የእይታ ቅንብር በመያዝ፤ ጉልህ ሆኖ እንዲታይ ወይም ልብ ይባል ዘንድ ለተመልካቹ ያቀርባል፡፡ ፎቶግራፍ ከአንድ ሂደታዊ አውድ ወይም ቀጣይነት ካለው ክስተት ተለይቶ የተያዘ ቅጽበት ነው። እስቲ ስንመለከተው የነበረን ፊልም ስናቆመው የሚከሰተውን ሁኔታ ለአፍታ እናስብ፤ ፊልሙን እንደገና እስከምናስጀምረው ድረስ በምናቆምበት ወቅት የታየው ቅጽበት ወይም ምስል በእይታነት ይቀጥላል፣ ነገር ግን ፊልሙ እንደገና እንደጀመረ ያ ቅጽበት ይጠፋና ቀጣዩ እይታ ይከሰታል። በሌላ በኩል ፎቶግራፍ ቀጣይ ሆኖ በሚመጣው ቅጽበት የመዋጥ ስጋት የለውም፡፡ በምንም ውስጥ ለረጅም ጊዜ ይኖራል፡፡ ይህ የዘለቄታነት ባህሪ የማይንቀሳቀሰውን ምስል ጎልቶና ገዝፎ እንዲታይ ያደርገዋል፡፡ ይህም ተንቀሳቃሽ ያልሆነ ምስል ባህሪ ተመልካቹ ተረጋግቶ በቅጽበት ኃላፊ የሆነውን የእይታ ልምድ በሚገባ እንዲያጤን ይረዳዋል ፡፡

In a world where the obvious often eludes our grasp, modern photography emerges as a crucial tool to decipher our surroundings. Mulugeta Ayene, an Ethiopian photojournalist and fine art photographer, masterfully captures these elusive moments. Residing in Addis Ababa, Ethiopia, Mulugeta's lens focuses on social transformations and their impact on identity and societal bonds.

His acute eye for pivotal moments earned him the first prize in the 2020 World Press Photo Contest's Spot News stories category. He was also a distinguished nominee for the World Press Photo of the Year and Story of the Year in 2020. Further honors include first prizes in the 'Excellence in Journalism' competition by the Foreign Correspondents Association of Ethiopia (FCAE) in 2011 and 2012 and the India-Africa Photo Contest in 2012.

Mulugeta's work, transcending mere visual documentation, invites us to delve deeper into each frame to unravel our time's fleeting yet profound narratives. His ability to capture the essence of a moment challenges viewers to reflect on the broader context of our ever-evolving world, encouraging a deeper appreciation of the complexities and nuances that define our collective journey.